Crossሃይማኖት/Faith

 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። 

ጸሎተ ሃይማኖት - ግእዝ 

ነአምን፡ በአሐዱ አምላክ፡ እግዚአብሔር አብ፡ አኀዜ ኵሉ፤ ገባሬ ሰማያት ወምድር፣ ዘያስተርኢ፥ ወዘኢያስተርኢ። 

ወነአምን፡ በእግዚአብሔር ወልድ፡ አሐዱ እግዚእ፣ ወልደ አብ ዋሕድ፣ ዘህልው ምስሌሁ፡ እምቅድመ ይትፈጠር ዓለም፤ ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ብርሃን፡ ዘእምብርሃን፣ አምላክ፡ ዘእምአምላክ ዘበአማን፤ ዘተወልደ፤ ወአኮ ዘተገብረ፤ ዘዕሩይ ምስለ አብ፡ በመለኮቱ፤ ዘቦቱ ኵሉ ኮነ፤ ወዘእንበሌሁሰ፡ አልቦ ዘኮነ፣ ወኢምንትኒ፡ ዘበሰማይኒ፥ ወዘበምድርኒ።

ዘበእንቲአነ ለሰብእ፣ ወበእንተ መድኃኒትነ፡ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ፤ ወተሠገወ፡ በግብረ መንፈስ ቅዱስ፣ እማርያም፡ እምቅድስት ድንግል፣ በነሢአ ሥጋ፡ እምሥጋሃ፥ ወነፍስ፡ እምነፍሳ፡ ኮነ ብእሴ ፍጹመ። በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ፡ ተሰቅለ፤ ወሓመ፤ ወሞተ፤ ወተቀብረ፡ በእንቲአነ፣ ወተንሥአ እሙታን፣ አመ ሣልስት ዕለት።

ዐርገ በስብሓት፡ ውስተ ሰማያት። ወነበረ፡ በየማነ አቡሁ፣ በመንበሩ ዘበዕሪና።

ዳግመ፡ ይመጽእ በስብሓት፤ ይኰንን፡ ሕያዋነ፥ ወሙታነ። ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ።

ወነአምን፡ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ። ውእቱ፡ መንፈሰ ጽድቅ፤ ማኅየዊ ዘበአማን፤ ዘሠረፀ እምአብ፣ ዘንሰግድ ሎቱ፣ ወንሰብሖ፡ ምስለ አብ፥ ወወልድ፣ ወዘነበበ በነቢያት፤ ዘወረደ ላዕለ ሓዋርያት፤ ወጸጋሁ ዘመልዓ ዓለመ፡ በቤዛ መስቀሉ፡ ለኢየሱስ ክርስቶስ።

ወነአምን፡ በአሓቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፡ እንተ ይእቲ ዘመሠረታ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ እምጥንት፥ በኪዳነ ልቦና፡ ዘሰብኣውያን ቀደምት፤ ወዘአጽንዓት፡ በቃለ ነቢያት፤ ወዘፈጸማ፡ በላዕለ ኵሉ ጕባኤ፡ ዘሓዋርያት። በውስቴታ፡ ያቄርቡ ካህናት፡ መሥዋዕተ ሥጋሁ ቅዱሰ፥ ወደሞ ክቡረ፡ ለኢየሱስ ክርስቶስ። ወባቲ ይትዌከፉ ምእመናን፥ ወምእመናት፡ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ፡ ዘዘዚአሁ።

ወነአምን፡ በአሓቲ ጥምቀት፡ ለሥርየተ ኃጢኣት።

ወነአምን፡ በትንሣኤ ሙታን፤ ወሕይወተ ዘለዓለም፤ ለዓለመ ዓለም፤ አሜን። 


   

ethiopic cross (343x640)

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። 

የሃይማኖት ጸሎት - አማርኛ 

ኹሉን በያዘ፣ ሰማይንና ምድርን፥ የሚታየውንና የማይታየውን በፈጠረ፡ አንድ አምላክ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። 

ዓለም ሳይፈጠር፡ ከእርሱ ጋራ በነበረ፥ አንድ የአብ ልጅ፥ አንድ ጌታ በሚኾን፡ በእግዚአብሔር ወልድም እናምናለን። እርሱም፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን፥ ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ፥ የተወለደ እንጂ፡ ያልተፈጠረ፣ በመለኮቱ፡ ከአብ ጋራ የሚተካከል፣ ኹሉ፡ በእርሱ የኾነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በሰማይ ካለው፣ በምድርም ካለው፡ ያለእርሱ፡ ምንም ምን፡ የኾነ የለም። 

ስለእኛ ስለሰዎች፥ እኛን ለማዳን፡ ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም፡ ከሥጋዋ፡ ሥጋ፥ ከነፍሷ፡ ነፍስ ነሥቶ፡ ፍጹም ሰውን ኾነ። በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን፡ ስለእኛ፡ መከራን ተቀበለ። ተሰቀለ። ሞተ። ተቀበረ። በሦስተኛውም ቀን፡ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። በክብር፥ በምስጋና፡ ወደሰማይ ዐረገ። በአባቱም ቀኝ፡ በዙፋኑ ተቀመጠ። ዳግመኛም፡ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ፡ በምስጋና ይመለሳል። ለመንግሥቱ፡ ፍጻሜ የለውም። 

በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እርሱም፡ ሕይወትን የሚሰጥ፣ ከአብ የሠረፀና በነቢያት ዐድሮ የተናገረው፥ በሓዋርያት ላይ የወረደውና በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት፡ ዓለሙን፡ በጸጋው የሞላው፡ ቅዱሱ የእውነት መንፈስ ነው። ለእርሱም፡ ከአብና ከወልድ ጋራ፡ በአንድነት እንሰግድለታለን፤ እናመሰግነዋለንም። 

ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ጥንት፡ በቀደሙት ሰዎች ኪዳነ ልቦና በመሠረታት፥ በነቢያት ቃል ባጸናትና በሓዋርያት ጕባኤ በፈጸማት፥  ካህናት፡ የእርሱን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም፡ ለመሥዋዕትነት በሚያቀርቡባት፥ ምእመናንና ምእመናትም፡ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋዎች በሚቀበሉባት፡ በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን። 

ኃጢኣት በሚሠረይባት፡ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። 

በሙታን ትንሣኤ፥ በዘለዓለምም ሕይወት እናምናለን። ለዘለዓለሙ፤ አሜን። 


 

ethiopic cross (343x640)

In The Name of The Father and of The Son and of The Holy Spirit One God Amen!

The Orthodox Creed

We believe in One God, God the Father, Almighty who possesses all, Maker of the Heavens and Earth, the visible and the invisible.  

We believe in God the Son, Jesus Christ, One Lord, the only begotten Son of the Father, who was with Him before the creation of the world.  He is Light from Light, True God from True God, begotten not made, and, in His Divine Essence, one with His Father. All things were made by Him, and without Him nothing whatsoever was made, in Heavens or on Earth.  

He came down from Heavens for our sake, for the sake of humanity, for our salvation. He was Incarnate in the womb of the Virgin Mary by the Divine Work of the Holy Spirit, and, acquiring the human soul and the human flesh from Her, became the Perfect Man.  

In the days of Pontius Pilate, He suffered, was crucified, died and was buried for our sake.  And He rose from the dead on the third day, ascended in glory into Heaven and sat on His Throne at the right-hand of His Father.  

He will come again in glory to judge the living and the dead.  There is no end to His Kingdom.

We believe in God the Holy Spirit.  He is the True and the life- giving Spirit who proceeds from God the Father, spoke through the Prophets, and, by the atonement of Jesus Christ, descended upon the Apostles and filled the world with His Grace. We worship and glorify Him with the Father and the Son.

We believe in One Holy, Catholic, and Apostolic Church that was founded by the Word of God, Jesus Christ, initially in the Hearts of the Patriarchs and Matriarchs, and later sustained by His Divine Messages through the Prophets, and finally brought to perfection through the Holy Spirit by His convocation of the Apostles, and where priests offer His Holy Body and Sacred Blood as Sacrifice for the Holy Communion with God, and where the Sacramental Blessings of the Holy Spirit are bestowed upon and communicated to all believers.  

We believe in One Baptism for the remission of sins.  

We believe in the Resurrection from the dead and the Life in Eternity, world without end.  Amen. 


ethiopic cross (343x640)