Author Archives: admin

“ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ” – June 18, 2016

“ወእምዝ ወጽአ ካልዕ አርዌ እምነ ምድር፤ ወበሥልጣኑ ለቀዳማዊ አርዌ ይገብር ኩሎ በቅድሜሁ፤ ወይረስያ ለምድር ከመ እለ ይነብሩ ውስቴታ ይሰግዱ ሎቱ ለቀዳማዊ አርዌ ” (ራዕይ 13፡12) ።

ሰሞኑን በቤተ ክርስቲያናችን ዙሪያ በውስጥና በውጭ የሚካሄደውን አየሁ። የሚንጫጫውንም ሰማሁ። ተጽፎ ባነበብኩትና በመገናኛ ዘዴዎች በሰማሁት ጫጫታወች ውስጥ ያለችውን ቤተ ክርስቲያንን እንዴት ልግለጻት ብየ አሰብኩ። በዚህ የሀሳብ ማእበል ውስጥ ሳለሁ፤ በአባይ በርሀ፤ በፊላው ስር ተከሰተ እየተባለ በልጅነቴ ሲነገር የሰማኌት ቀውጢ ትዝ አለችኝ። በዚያች ቅጽበት በተከሰተችው ቀውጢ ክስተት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያኔን አየኋት። ሙሊውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ሌላም አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ”

በመፈተን ላይ ያለችው የከንሳስ መድኃኔ የኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ በዓል አከበረች።

በመፈተን ላይ ያለችው የከንሳስ መድኃኔ የኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ በዓል አከበረች።

ከከንሳስ ደብረ ሣሕል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን

ፈተናው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ከኛ ያልተለዩ ን የዲሲው ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መምህር አባ መአዛ እና፤  የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን መምህር አባ ኃይለ ሚካኤል  ሚያዝያ 1 ቀን ዓርብ ቀደም ብለው ለበዓለ ንግሡ ወደ ከንሳስ መጡ። ቅዳሜ ሚያዚያ 2  ጧት ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ውለታ የዋሉት Father Piosis Alex የቆረቆሩትን ገዳም  አብረን ጎበኘን።  በጉብኝቱ ወቅት ቀሲስ አስተርአየ  Father Piosis Alex  ለኢትዮጵኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን የሰሩትን ውለታ በማውሳት ሚከተለውን ትዝታ ተናገሩ።

የቀሲስ አስተርአየ  ንግግር

የደርግ መንግሥት ፈርሶ ኢትዮጵያ በወያኔዎች እጅ ስትወድቅ፤  አቡነ መርቆርዮስና አቡና ዜና ተከታትለው   ወደ ኬንያ ተሰደዱ። መሰደዳቸውን ስሰማ በኬንያ በነበርኩበት ትምህርት ቤት ከኔ ጋራ ይማሩ የነበሩት ኬንያውን፤ በዚያ ወቅት በኬንያ ውስጥ በ PARA Government  እና PARA church ድርጅቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ኬንያውያን እና፤ በአሜሪካም  Father Piosis Alex ሌሎችም በስያትል  በኦሬገን በፖርት ላንድ  በካሊፎርንያ በአትላንታና በሙዙሪያ ይኖሩ የነበሩ፤  brotherhood በሚባል ድርጅት ስም  ይንቀሳቀሱ የነበሩ ክርስቲያኖችና  የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ንብረታቸውን በማቅረብ እያከታተሉም በናይሮቢ ለሚገኘው ለአሜሪካ ኤምባሲ ጽ/ ቤት ባቀረቡት ጥያቄ በመጀመሪያ አቡነ ዜና ወደ ስያትል ገቡ። ቀጥለውም አቡነ መርቆርዮስ ወደ ስያትል እንዲገቡ ረዱ። በሴንት ሉስ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያንም በሳቸው ጓደኛ በFather Moses አሳሳቢነትና አጋዥነት ሲሆን።  በከንሳስ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያኖቻችም በFather Piosis Alex ጋባዥነት ወደካንሳ  መጥቼ ባገኘኌቸው በነ ወይዘሮ አሰለፈች። ወይዘሮ ነገደና በሞት የተለዩን ወይዘሮ አዛለች ነው። የ Father Piosis Alex ውለታቸው የሚዘነጋ አይደለም” ካሉ በኋላ Father Piosis Alexም  የሚከተለውን ተናገሩ።

Father Piosis Alex ንግግር

ከቀሲስ አስተርአየ ጋራ በነበራቸው  ጓደኝነትና ፍቅር ቀሲስ አስተርአየ የተናገሩትንና ሌላም ከቀሲስ አስተርአየ ጋራ ሌሎ ችም ብዙ ነገሮ ች ተካፈለናል። ወደፊትም ባለብን ክርስቲያናዊ ሀላፊነት አቅማችን የፈቀደልንን ሁሉ በጎ ነገር እናደርጋለን ካሉ በኋላ የማህበር ጸሎት ተካፈልን።  በገዳሙ ቤተ ማእድ ጸበል ጸሪቅ ከተካፈልን በኋላ፤  የገዳሙን ንብረት ሁለት ጋሻ መሬትና ያላቸውን ረዥምና አጭር እቅድ ገልጸውልን በሰላም በፍቅር ሽኝተውናል።

ማታ ጥንተ ስቅለቱንና ትንሳዔውን በማስታወስ የምሕላ ጸሎት ተደርሶ የተጀመረው ቅዳሜ ማታ የተጀመረው የበዓሉ ስርአት፤  አምና በዓርብ በርሀ ለታረዱትና አሁንም በውስጥም በውጭም  በመሞት ላይ ላሉት ያሉትን ወገኖቻችን በማሰብ፤  ጸሎተ ቅዳሴው በአባ ኃይ ለ ሚካኤል ተከናውኖ፤ የዕለቱ ትምህርት በአባ መአዛ ከተሰጠ በኌላ፤ በታቦተ ህጉ ዑደት ስርአ በዓሉ ተፈጽሟል።

የእግዚአብሔር ሕግጋት (አሰርቱ ቃላት) የተጻበት ጽላት ያለበትን ታቦት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከሌሎች በዓለም ካሉት አብያተ ክርስቲያናት በተለየ መንገድ  ለምን እንደምትጠቀምበት ለመረዳት ከፈለጉ፤  ቀሲስ አስተርአየ   ስለጥምቀት በዓል “ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው ሕግጋቶች” በሚል  ርእስ  ጥር ፩ ፳፻፮ ዓ.ም. የጻፉትን  ጦማር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ደብረ ዘይት – ስብከት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ April 3, 2016

ፍካሬ ኢየሱስ

መጋቢት 25 ቀን 2008 ዓ. ም.

      ይህ ሳምንት ጾመ ኢየሱስን ለጀመርንለት ወቅት አምስተኛው ሳምንት መሆኑ ነው። እንደሌሎች ሳምንታት ልዩ መጠሪያና መታወቂያ ስም አለው።  ደብረ ዘይት ይባላል። ደብረ ዘይት ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ ነው። “በስመ ሀዳሪ ይጼዋእ ማህደር” እንዲል፤ ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ ለተፈጸመው ክስተት መጠሪያ ሆኗል። አገራችን ኢትዮጵያ፤  እኛ ኢትዮጵያውያን ዜጎቿ በተከሰትንባት ኢትዮጵያ እንደተባለች ማለት ነው። በዚህ ልማድ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ፤  ለክስተቱ ወይም ለፍካሬ ኢየሱሱ፤ ደብረ ዘይት የተባለው ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ  መጠሪያ እንዲሆነው አድርጓል።

ይሁን እንጅ በከፍተኛው ትምህርት ቤቶቻችን የሚጠራበት የውስጥ ስም  አለው። ይህም በደብረ ዘይት ላይ የተከሰተው  ፍካሬ  ኢየሱስ ነው።

ከዚህ ቀደም ቀሲስ አስተርአየ ገጠመኞችን እያንጸባረቁ  በተለያዩ  ጊዜዎች ስለ ደብረ ዘይትና ስለ ፍካሬ ኢየሱስ፦

1ኛ፦ ”ኢትዮጵያ በሶስቱ ፍካሬዎች“ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ/ም

2ኛ፦ ደብረ ዘይትና አባ ማትያስ “ዘያነብብ ለይለቡ (አንባቢ ያስተውል!)” (ማቴዎስ ፳፬፡፲፭) ሚያዝያ ፳፻፭ ዓ.ም

3ኛ፦ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም” ሰኔ ፳፻፭ ዓ.ም. ጦማሮች አቅርበው በተለያዩ   ድረ ገጾች በሰፊው ተነበዋል።

ዘንድሮም ከዚህ ቀደም በጽሁፍ ያቀረቧቸውን ሁሉ ጦማሮች በቪድዮ እንዲቀርቡ ከቅርብም በሩቅም  ከሚኖሩ ምእመናን በቀረበልን ጥያቄ መሰረት፤  ካካባቢያችን ራቅ ባሉ ስቴቶች  የሚኖሩ  ሁለት ወንድሞች  ከፍተኛውን አስተዋጽኦ  በማድረግ ስላገዙን  የቪድዮ ካሜራ ልንገዛ ችለናል። ለሁለት ሳምንታት የቀረቡት ትምህርቶች ለሙከራ ያህል በቪዲዮ ተቀድተው ተለቀዋል።  ከፍተኛውን ዋጋ የረዱንን ሁለት ወንድሞቻችንንም እያመሰግን  በመጻጉዕና በፍካሬ ኢየሱስ ላይ የቀረቡት እነዚህ ትምህርቶችን አቅርበናልና ከዚህ በታች ይመልከቱ፤ ቅን እርማተዎ፥  አስተያየተዎና  ድጋፍዎ እንዳይለየን በትህትና እንጠይቃለን። ለዚህ ዓመት ላደረሰን አምላክ  ክብር ምስገና ይግባው! አሜን።

የከንሳስ  ደብረ ሣሕል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን።

 

በካንሳስ ደብረ ሣሕል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።
መነሻ ጥቅስ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከቁጥር 1 – 35

ቦካሳ

በዚህ ዘመን፤ እንደ ጥንቱ ክርስቲያኖች፤ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንና ለኢትዮጵያ፤ እንደ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  የሚወዱትና የሚያምኑት ሰው ማግኘት የፈጣሪ ቡራኬ ነው። ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  በተለያየ ምክንያት በስሕተት ጎዳና  ያሉትን ሰዎች እውነቱን ለማስረዳት በሊቅነታቸው በሚሰጠ እጅግ ጠንካራ ተግሣጽና ምክር መንፈሳዊ ሕይወታችንን ከፍ ስለሚያደርጉ ክብር ገባቸል።

“ፈታኝና አስቸጋሪ ነገር ሲገጥመኝ ለመግለጽ  የምሞክረው  በቤተ ክርስቲያናችን ሕጽን የነበሩ ሊቃውንት አበው ኢትዮጵያ  ባቋረጠችባቸው ዘመናት ያጋጠሟትን መከራና ደስታ በገለጹባቸው በቅኔወቻቸውና በስሜታቸው ነው። ስህተት መሆኑን ህሊናየ ከነገረኝ፤  እውነት አለመሆኑን እያወኩ የዘመኑ ሰው ስለማይወደው ይጠላኛል፤ ይሸሸኛል፤ ይርቀኛል፤ ይዘልፈኛል ብየ ከመናገር አንደበቴን አልገታም።  ከንቱ ውዳሴና ክብር ለማግኘት፤  የከንቱ ውዳሴና ክብር ትርፍ ምንጭ ከሆኑት ዘመናውያንና ብዙ ቍጥር ከሚያጅባቸው ጋራ በመሰለፍ ከማገኘው ክብር፤ ሽልማትም ሆነ ሹመት ፤ ምንጫቸውን ሞት ካደረቀባቸው፤ ሊረዱኝና ሊደግፉኝ ሞት ከከለከላቸው ፤ በህይወት ከሌሉ  ሰዎች ጋራ መሰለፉን እመርጣለሁ። ሰማይ ዝቅ መሬት ከፍ ቢል፤ ሊቃውንት ለማይቀበሉት ፤ ቤተ ክርስቲያንን ፣ ኢትዮጵዮጵያአገርንና ወገንን ለሚጎዳ ነገር ህሊናየን  መቃብር ማድረግ ፈጽሞ  አልፈልግም።” (ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ) 02/20/2016

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል

“ድንበር ሲፈርስ፤ መሐሉ ዳር ይሆናል” በሚል ርእስ ይህች ጦማር የፈለቀችበት ዘመን፤ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገር የሚያዋስኗት ድንበሮችና፤ በውስጥም ዜጎቿ ተከባብረውና ተዋደው የሚኖሩባቸው ወሰኖች የፈረሱበት፤ ረዥም ዘመን የኖሩ ዛፎች የተጨፈጨቡት፤ መልሰው እንዳያቆጠቁጡ፤ (እንዳያንሰራሩ) ግንዶች ከነስራቸው የነገሉበት ዘመን ነው። ለ 25 ዓመት ኢትዮጵያን የገዛው የወያኔ መንግሥት፤ አገሪቱን ከተቆጣጠረበት ቅጽበት ጀምሮ በቅርብ የሚታየው ከሩቅ የሚሰማው መፍረስና መገሰስ ቢሆንም፤ በየዘመኑ ድንበር እየጣሱ ከመጡ ወራሪዎች ጋራ ለዳር ድንበር ስትፋለም የኖረች ጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ወቅት ምን ትላለች?የሚለው ጥያቄ በኢትዮጵያውያን መካከል ብቻ ሳይወሰን፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በሚያውቁ በውጭ አገር ሊቃውንት መካከልም መነጋገሪያ ሆኗል።
በዚህ ወቅት የፈለቀችው ይህች ጦማር፤ ይህች ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ድንበር የተሸከመችው ሀሳብ የራሴ ፈጠራ አይደለም። በሱባዔ፣ በህልም የተከሰተልኝ አይደለም።አልበቃሁምና መንፈስ ቅዱስ ገለጾልኝም አይደለም። የቅኔ ችሎታቸውን ከመንደር ቧልትና ነገረ ዘርቅ ያላቀቁ ሊቃውንት የህዝቡን አሉታ እየተመለከቱ፤ በሰረዙ ቅኔያቸው ሲዘርፉበት የሰማሁት ነው። የትርጓሜ መምህራንም ባንድምታ ትርጉማቸው የሚያመሠጥሩት፤ ለእለታዊ ጥቅም ተልእኳቸውን ያልሸጡ ቀሳውስትም በጸሎታቸው ሲገልጹት የሰማሁትና “ድንበር ሲፈርስ መሐሉ ዳር ይሆናል፤ የዛፍ ጫፉ ሲጨፈጨፍ ግንዱ ጫፍ ይሆናል”እያሉ የመንደር አዛውንትም ሲናገሩ የሰማሁትን ነው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

1 2 3 4 5 9