Author Archives: admin

ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ላወጁት የተሳሳተ ትምህርት መልስ

ትድረሳችሁ

ከእውቀቱ፤ ከችሎታው፤ ከስሜቱና ከፍላጎቱ ጋራ፤ በአገር ውስጥና በውጭ በገጠር በከተማ በየአድባራቱና ገዳማቱ ላላችሁ ሁሉ፤ ተሐድሶዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ላወጁት የተሳሳተ ትምህርት መልስ ይሆን ዘንድ ላቀረብኳት የምስክርነት ጦማር መግቢያ ትሆነኝ ዘንድ ለሁለተኛ ጊዜ በግእዝ የጻፍኳት ይህች ጦማር ትድረሳችሁ። “ለሁለተኛ ጊዜ” ያልኩበት ምክንያት ከዚህ በፊት አቡነ ቀውስጦ ወደ ዲሲ በመጡበት ወቅት፤ ስለቤተክርስቲያናችን ጠቅላላ ችግር በግእዝ አዘጋጅቼ ሰጥቻቸው ነበርና ይህችኛዋ ሁለተኛ በመሆኗ ነው። አቡነ ቀውስጦስ “ቤተ ክርስቲያናችን ካስተማረችህ አንዱ ነህ። ወደውጭ ወጥተህም የውጩን ለመቃኘት እድሉን አግኝተሀል። በዚህ ላይ ከሁሉም ቀደም ብለህ ወደ አሜሪካ በመምጣትህ ብዙ አይተሀል። ታዝበሀልም። አሁን ወደ ዲስ መጥቻለሁና፤ የታዘብከውንና ለቤተ ክርስቲያን ይጠቅማል የምትለውን በጽሑፍ አርገህ አቀብለኝ” ብለውኝ በወቅቱ የታየኝ የተሰማኝን ግንቦት 24 ቀን 1997 ዓ/ ም ጽፌ አቀበልኴቸው። ይዘውት ወደ አዲስ አበባ ሄደው ሲመለሱ ምን ይዘው እንደተመለሱ ጠየኳቸው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ደመራ (New: 9/27/2015)

እንኳን ለዘንድሮው የደመራ በዓል አደረሳችሁ! አደረሰን!

ሰላሙ የደፈረሰበት ህዝብ የመንፈስ ጤንነት አይሰማውም። ሰላምና ጤና የሚነጣጠሉ አይደሉምና፤ የመንፈስ ጤንነት የደፈረሰበት ህዝብ ጤናማ ነው ማለት አይቻልም። “ሰላም ሳይኖር ሰላም የሚሉ ወዮላቸው!” ከሚለው ከነብያት ቃል ጋራ ተጋጨ። ይህም ብቻ አይደለም። ሰላም የሌለን ቄሶች ሰላም እንደሌለን እያወቅን፤ የተቀጠርንለት እለታዊ ገቢያችን እንዳይቀርብን “ ሰላም ለኩልክሙ” እንላለን። በጥቅሉ ልማድ አድራሾች ሆን። የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ነን የምንል ኢትዮጵያውያን ሰላም ምንጭ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሊወሀደን ቀርቶ አልተቀበልነውም። ከዚህ ዓመት የደረስነው አሁን ያለንበት “በደብረ ሰላም ኢይኩን ሀከክ” ማለትም፦ በደብራችን ህውከት ብጥብጥ አይኑር” እያልን ጉሮሯችን እስኪሰነጠቅ የምንጮኸው ላምድ ለማድረስ ብቻ ነው። ስለዚህ “እንኳን አደረሳችሁ” እንጅ “እንኳን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ” ማለት መዋሸት ነው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

ፍልሰታ “እኛም ማየት አለብን” – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

filsetaእመቤታችን በጥር ወር አርፋ እስከ ነሐሴ ሳትቀበር ቆይታ፥ በነሐሴ ወር አካሏ ከነበረበት ቦታ ፈልሶ ከዚህ ዓለም ለቃ ማረጓን ለማመልከት ‘ፍልሰታ’ ተባለች:: ይህች ጾም “እኛም ማየት አለብን” ከሚል ጠንካራ ሰባዊ ምኞትና መንፈሳዊ ውሳኔ ከሐዋርያት የፈለቀች ናት:: ታሪካዊ መሠረቷ፥ ከእመቤታችን እረፍት በፊት ቀደም ብሎ ክርስቶስ ተሰቅሎ ሞቶ በተቀበረበት ጊዜ፥ የክርስቶስን ትንሣኤ ለማስተባበል “እኛ ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት ሰረቁት” (ማቴ ፳፰፡፲፪) ብለው ሐሰት እንዳሰራጩ ሁሉ፥ አሁንም እመቤታችን በሞተችበት ጊዜ፥ ሐዋርያት ሬሳዋን ለመቅበር ይዘው ወደ መቃብር ሲጓዙ፥ የክርስትናን መስፋፋት ለማዳፈን ይጥሩ የነበሩ ሰዎች የእመቤታችንን አካል ነጥቀው ለማቃጠል ሞከሩ:: በእግዚአብሔር ረድዔት የእመቤታችን አካል ከመቃጠል ተጠብቆ የቆየበትን ሁኔታና ቦታ ከዮሐንስ በቀር ሐዋርያት አላወቁም ነበር:: ሐዋርያት እንደ ዮሐንስ እስከ መጨረሻ ጸንቶ መቆም አቅቷቸው ጥለው በመሸሻቸው በመጨረሻ የሆነውን አላዩም ነበረና፥ ወስደው አቃጥለውት ይሆን? በሚል ጭንቀት ላይ ወደቁ:: ዮሐንስ አልተቃጠለም አይቻለሁ ብሎ ነገራቸው:: ዮሐንስ ያየውን “እኛም ማየት አለብን” ብለው ሐዋርያት ለማየት ወሰኑ:: ለማየት የሚያስችላቸው መስኮት፥ ሱባዔ መግባት ነበርና ከነሐሴ ፩ ቀን ለሁለት ሱባዔዎች በጾም በጸሎት ራሳቸውን አገለሉ:: የተመኙትን የፈለጉትን ማግኘትና ማየት ብቻ ሳይሆን ከማየትም አልፈው ደቂቀ አዳም የሚነሳበትን ቀን ሳትጠብቅ በልጇ ስልጣን እንዳረገች ተረዱ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የዘንዶ ሱባዔ?

ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን የሶስቱም ማለትም የሰአት፤ የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው። ሱባዔ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ፤ ረቂቅና ምጡቅ ግንዛቤ አለው። በመንፈሳችንና በሥጋችን መካከል ያለውን ሚዛን አለመሰበሩንና አለማጋደሉን፤ በፈጣሪያችንና በራሳችን መካከል፤ በህዝባችንና በራሳችን መካከል ያለንን ግንኙነት የምንፈትሽበት ነው። በሩቅና በቅርብ ያለውን አካባቢያችንን ማየት የምንችልበት ተራራ ነው። ውስጣዊ ህሊናችንን የምናይበት ረቂቅ መስታወት ነው። የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የሚያሳየን፤
እመቀ እመቃት፡ አየረ አየራት፡ ያሉትን ሁሉ ፍጥረታት የምንፈትሽበት ተራዛሚ መነጽር ነው።

ሱባዔ፦ በሰው ብቻ የተወሰነ አይደለም። በደማቸው ሞቃትነትና ቀዝቃዛነት የሚለያዩ ፍጥረታት በየደረጃቸው ሱባዔ ይገባሉ። የፍጥረታትን ቅደም ተከተል በመጠበቅ የደመ ሞቃት እንስሳትንና፤ የዘንዶን ሱባዔ ከዳሰሰን በኌላ፤ የዘመናችን በተለይም የመነኮሳት ሱባኤ ከጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሱባዔ ተቀይሮ፤ ከደመ ሞቃት እንስሳት ምን ያህል እንደራቀና ወደ ዘንዶ ሱባዔ እንደተቀረ በማነጻጸር፤ ይህ የዘንዶ አይነት ሡባዔ የማይታረም ባለበት የሚቀጥል ከሆነ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ሁሉ ወንዱም ሴቱም በተለይ ትዳር ያፈረሰ በዝሙት በሌብነት በዘራፊነት የተከሰሰ ሁሉ ቆቡን እያጠለቀ፤ ምንኩስና ቁምስና ወደ ተላበሰ ቅስናና ሊቀ ጳጳስና እኛም እንግባ ብሎ መነሳቱ መፍትሄው ይመስለኛል። ሁሉንም አይተን ከምዳሜ ለመድረስ ከደመ ሞቃት እንስሳት ሱባዔ እጀምራለሁ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ”

የግእዙ ትርጉም

“ትእይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩክ ወድቀ ላእሌየ። ወኩሉ ዘተጽሕፈ ለተግሳጸ ዚአነ ተጽሕፈ ከመ በትእግስትነ ወበተወክሎ መጻሕፍት ንርከብ ተስፋነ”(ሮሜ 15፡ 3)።

ይህችን ጦማር “የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ” በምትለው ሐረግ ላይ እንድመሰረትታ ያደረገኝ ተጽፎ ከቆየው መጽሐፍ በመፍለቋ ነው። የፈለቀችበት መጽሐፍ ጨካኞች በዜጎቻቸው ላይ መከራ በሚያበዙበት ወቅት መንፈሳቸውን በጽናት በተስፋና በስነ ምግባር እንዲያጠነክሩ የሚያሳስብ ነው። “የተጻፈ ለተግሳጽና ለትምህርት ተጻፈ” የምትለው ጥቅስ ለዚህች ጦማር ምክንያት የሆነችውን ጥንታዊት ክርታስ አጉልታ ስለምታሳይ ከቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ወስድኳት። ይህችን ጥንታዊት ክርታስ ያቀበሉኝ ዶ ክተር ጌታቸው ኃይሌ ናቸው። “የታረዱት ነፍሳት ጩኸት” በሚል ርዕስ ከተባበሩት መንፈሳውያን ህብረት መግለጫ በሚመለከቱበት ወቅት እንዳጋጣሚ ከዚህ በታች የሰፈረችውን ክርታስ የያዘውን መጽሐፍ ይመለከቱ ስለነበር፤ ከተባባሩት መንፈሳውያን ህብረት መግለጫ ጋራ መመሳሰሏ ገርሟቸው ይህችን ክርታስ እንድመለከታት ከመጽሐፉ ቆንጥረው አቀበሉኝ።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ፓትርያርክ፤ሊቃነ ጳጳሳት፤መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ

ለዚህች ጦማር መፍለቅ ምክንያት የሆነው ባለፈው እሁድ ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ/ ም ያከብረነው ጰራቅሊጦስ የሚባለው ዓመታዊ በዓል ነው። በዚህች ቀን ጰራቅሊጦስ (እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ) ቤተ ክርስቲያንን በምድር ላይ የመሰረተበትን ዓላማና ተግባር እናጤናለን። ዓላማው፤ ሐዋርያት ከክርስቶስ ጋራ በቆዩበት ጊዜ የተማሩትንና የሰሙትን እንዳይረሱ፤ በጥበብ በማስተዋል በቅድስናና በድፍረት ሰውን ከሀሰት ወደ እውነት፤ ከክህደት ወደ እምነት፤ ከበደል ወደ ደግነት፤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፤ ከግለኝነት ወደ ህዝባዊነት፤ በጠቅላላው ከዲያብሎስ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ነው። እነዚህን ነገሮች በተግባር የሚያውሉት ሰዎች ክርስቲያኖች ተባሉ። ከክርስቲያኖች መካከል በእውቀታቸው፤ በችሎታቸውና በመንፈሳዊነታቸው ተመርጠው በአመራር ላይ ያሉ ደግሞ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተባሉ። የነዚህ ሁሉ ክምችት ቤተ ክርስቲያን ተባለች። ይህች ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች “ትምጣ” እያልን የምንመኛትን በሰማይ ያለችውን መለኮታዊት መንግሥት የምታንጸባርቅ ምሳሌና ምልክት የሆነች ድርጅት ናት።

ይህችን ድርጅት በመጀመሪያ ተቀበሉት ተብለው ከሚነገርላቸው ህዝቦች መካከል ኢትዮጵያውያን አሉበት። በዚህም ምክንያት ያብነት መምህራን ኢትዮጵያውያንና የሚኑሩባትን ምድር እንደሚከተለው ይገልጿቸዋል። ኢትዮጵያውያን ፊደሎች ናቸው። ኢትዮጵያ ደግሞ የፊደል ገበታቸው ናት። ኢትዮጵያውያን ታቦቶች ናቸው። ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት ምድር ለኢትዮጵያውያን መንበራቸው ናት።ከፊደል ገበታ ያልተሳተፈ መጽሐፍ ማንበብ እንደማይችል፤ ከኢትዮጵያዊነት ስሜትና መንፈስ ያልተሳተፈ ኢትዮጵያን አያውቃትም። በኢትዮጵያዊነት
ያልተቀረጸም፤ ኢትዮጵያን መንበሩ ሊያደርጋት አይችልም ይላሉ። ስለ በዓለ ጰራቅሊጦስ አጭር መግለጫ ከሰጠሁ በኋላ፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውን የፊደል ገበታቸው፤ የተቀመጡባት መንበራቸው እንደሆነችና፤ ቤተ ክርስቲያን በመሬት ከተመሰረተችባቸው አገሮች አንዷ እንደሆነች ለመግለጽ እሞክርና፤ በዘመናችን በተለይም በወያኔ ዘመን ያየናቸውን መንፈሳውያን መሪዎች በየትኛው መንገድ ላይ እንዳሉ በንጽጽር ለማሳየት፤ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አንቀጾች ይህችን ጦማር አቅርቤያታለሁ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

1 2 3 4 5 6 9