Category Archives: Kesis Asteraye’s Page

ሕዝበ ክርስቲያን በጰራቅሊጦስ መንገድ ሲሄዱ፤ፓትርያርክ፤ሊቃነ ጳጳሳት፤መነኮሳትና ቀሳውስት በሳጥናኤል መንገድ ነጎዱ

ለዚህች ጦማር መፍለቅ ምክንያት የሆነው ባለፈው እሁድ ሰኔ ፩ ቀን ፳፻፮ ዓ/ ም ያከብረነው ጰራቅሊጦስ የሚባለው ዓመታዊ በዓል ነው። በዚህች ቀን ጰራቅሊጦስ (እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ) ቤተ ክርስቲያንን በምድር ላይ የመሰረተበትን ዓላማና ተግባር እናጤናለን። ዓላማው፤ ሐዋርያት ከክርስቶስ ጋራ በቆዩበት ጊዜ የተማሩትንና የሰሙትን እንዳይረሱ፤ በጥበብ በማስተዋል በቅድስናና በድፍረት ሰውን ከሀሰት ወደ እውነት፤ ከክህደት ወደ እምነት፤ ከበደል ወደ ደግነት፤ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ፤ ከግለኝነት ወደ ህዝባዊነት፤ በጠቅላላው ከዲያብሎስ ወደ ክርስቶስ ለማምጣት ነው። እነዚህን ነገሮች በተግባር የሚያውሉት ሰዎች ክርስቲያኖች ተባሉ። ከክርስቲያኖች መካከል በእውቀታቸው፤ በችሎታቸውና በመንፈሳዊነታቸው ተመርጠው በአመራር ላይ ያሉ ደግሞ ጳጳሳትና ቀሳውስት ተባሉ። የነዚህ ሁሉ ክምችት ቤተ ክርስቲያን ተባለች። ይህች ቤተ ክርስቲያን በምድር ያለች “ትምጣ” እያልን የምንመኛትን በሰማይ ያለችውን መለኮታዊት መንግሥት የምታንጸባርቅ ምሳሌና ምልክት የሆነች ድርጅት ናት።

ይህችን ድርጅት በመጀመሪያ ተቀበሉት ተብለው ከሚነገርላቸው ህዝቦች መካከል ኢትዮጵያውያን አሉበት። በዚህም ምክንያት ያብነት መምህራን ኢትዮጵያውያንና የሚኑሩባትን ምድር እንደሚከተለው ይገልጿቸዋል። ኢትዮጵያውያን ፊደሎች ናቸው። ኢትዮጵያ ደግሞ የፊደል ገበታቸው ናት። ኢትዮጵያውያን ታቦቶች ናቸው። ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት ምድር ለኢትዮጵያውያን መንበራቸው ናት።ከፊደል ገበታ ያልተሳተፈ መጽሐፍ ማንበብ እንደማይችል፤ ከኢትዮጵያዊነት ስሜትና መንፈስ ያልተሳተፈ ኢትዮጵያን አያውቃትም። በኢትዮጵያዊነት
ያልተቀረጸም፤ ኢትዮጵያን መንበሩ ሊያደርጋት አይችልም ይላሉ። ስለ በዓለ ጰራቅሊጦስ አጭር መግለጫ ከሰጠሁ በኋላ፡ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያውን የፊደል ገበታቸው፤ የተቀመጡባት መንበራቸው እንደሆነችና፤ ቤተ ክርስቲያን በመሬት ከተመሰረተችባቸው አገሮች አንዷ እንደሆነች ለመግለጽ እሞክርና፤ በዘመናችን በተለይም በወያኔ ዘመን ያየናቸውን መንፈሳውያን መሪዎች በየትኛው መንገድ ላይ እንዳሉ በንጽጽር ለማሳየት፤ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት አንቀጾች ይህችን ጦማር አቅርቤያታለሁ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ” ከእውነት ጋራ የሚጋጭ ነገር እየሰራን ለመኖር አንድፈር

ይህችን ጦማር “ኢንሔሊ ተቃርኖተ ጽድቅ” በሚል ርእስ ለማዘጋጀት ምክንያት የሆነኝ፤ አቡነ ማትያስ የዘንድሮውን (የ ፳፻፮ ዓ.ም.) ትንሳኤን ምክንያት አድርገው ልጆቼ እያሉ
ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ያቀረቡት መልእክት ሲሆን፤ አንብቤ የተሰማኝን ሀሳብ እንድሰጥ ጥያቄ ስለቀረበልኝ ነው። ሳነበው በቅኔ ትምህርት ቤት ሳለሁ ባካባቢው ተከስቶ የነበረውን ነገር አሰታወሰኝ። ትዝታው ይህ ነው። በዋዛ በፈዛዛ ህይወቱን በማሳለፍ ላይ የነበረ አንድ ሰው ያባቱን መሬት ማረስ ረስቶ ያውሬ መፈንጫ እንዲሆን አደረገው። አጎቱ ታታሪ ሰራተኛ ነበሩና እሱ የረሳውን ደክመው አለሙት። ደክመው ካለሙት በኋላ፤ ይህ ቁም ነገር የለሽ ሰው “ያባቴ መሬት ይመለሰልኝ” ብሎ አጎቱን ባደባባይ ከሰሳቸው። እንዲመልሱለት የከሰሳቸው አጎቱ፤ በታታሪነታቸው በአራሽነታቸው ለምሳሌ የሚጠቀሱ፤ በዘመኑ በነበረው የእውቀት ደረጃም እጅግ የተማሩ፤ የተከበሩ ዳዊት ደጋሚ ነበሩ። ተከስሰው በቆሙበት አደባባይ ስለ ከሰሳቸው ሰው የሚከተለውን ተናገሩ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ጸርሁ በዓቢይ ቃል”: የታረዱት ነፍሳት ጩኸት – ዋሺንግተን ዲሲ በተደረገው ትዕይንት ላይ የቀረበ – በቀሲስ አስተርኣየ ጽጌ

“ጸርሁ በዓቢይ ቃል”: የታረዱት ነፍሳት ጩኸት! click here to open in new tab

Download the PDF file .


Download ““ጸርሁ በዓቢይ ቃል”: የታረዱት ነፍሳት ጩኸት!” -በግዕ-2.pdf – Downloaded 329 times – 316 kB

እርም (ሐራም)

በባህላችን የሰው ስም በትርጉም አልባነት እንደማይለጠፍ፤ ከሰውነታችን ጋራ የሚገናኙ ነገሮችም ስማቸው ከመነሻቸው ጋራ የተያያዘ ነው። “እንጀራ” ከምድራዊ ህይወታችን ጋራ ከተገናኙት መሠረታውያን ነገሮች አንዱ ነው። እንጀራ እስካሁን ድረስ የተነሳበትን የታሪክ ትዝታ ተሸክሞ ብዙ ዘመን ተጉዟል። እንጀራ ከወላጅ እናቱ ከጤፍ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ሩቅና ጥልቅ ትስስር እንዳለው ሁሉ፤ ከመብላት ስሜትና ሱስ ጋራ ተዋህዶ በሰውነታችን ስለጋባ፤ ዝንት ዓለም የኖረ ይህን ጥብቅ ግንኙነት የሚያስለቅቅ፤ ጥብቅ ምክንያት መቅረብ ያለበት ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ እየተጫነ የሚመጣውን እንጀራ አትብሉ ወደሚለው ሀሳብ ምን እንደወሰደን በግልጽ ለማቅረብና፤ እንዴትስ እናቁም ወደ ሚለው ውይይት ለመግባት፤ ከጉባዔ ትምህርት ቤት መምህራን የሰማሁትን ለውይይታችን መንደርደሪያ ብናድርገው የሚጠቅም ይመስለኛል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

እግዚአብሔር ያሳየዎ: ክርስቶስ ያመልክተዎ!

ማህበረ ቅዱሳንና አባማትያስ
እግዚአብሔር በሚያሳየው ክርስቶስ በሚያመለክተው መስመር የማይሰለፍ፤ በቡድንና በጥቅም በተራቆተ ስሜት ተሳስሮና ተለባብሶ የሚኖር ህብረተሰብ፤ ከራሱ በሚፈልቅ ስሜት ወይም ከውጭ በሚመጣ ግፊት ከመጠፋፋት ቢያመልጥም፣ ከመለያየት ማምለጥ ፈጽሞ አይችልም። ክርስቶስም “እርስ በርስዋ የምትለያይ አገር ሁሉ ትጠፋለች። እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት አይቆምም” (ማቴ 12።5)በማለት አስጠንቅቋል። ፍረዱብን እያሉ ተቆራኝተው ሰሞኑን ወደኛ በቀረቡት በማህበረ ቅዱሳንና በአባማትያስ መካከል የተከሰተው ይህ ነው። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዘዳግም!

ሙሴ አራቱን የኦሪት መጻሕፍት ከጻፈ በኋላ፤ በአራቱም መጻሕት የገለጻቸውን ጠቅለል አድርጎ በድጋሚ ያቀረበበት አምስተኛው መጽሐፍ ዘዳግም ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነውን ለማስወገድ የገለጸባቸውን ኃይለ ቃላት ለማስጨበት “አማን አማን እብለክሙ” እያለ በመደጋጋም ተናግሯል። በጸሎተ ቅዳሴያችንም “ተንስኡ ለጸሎት” የሚለውን እንደጋግማለን። ቃጭልም በመደጋገም እናቃጭላለን። የሚደጋገሙበት ምክንያት፤ የሰው ቀልብ ባዘነጊ ነገር በፍጥነት ይሰረቃል። ለዘላቂ ህይወቱ ተጻራሪና ከንቱ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ተንሸራቶ ስለሚገባ፤ ቀልቡንና ትኩረቱን ለመጠበቅ ነው። እንደዚሁ ሁሉ፤ እኔም አባቶቻችን የገጠማቸውን ችግር መፍቻ አድርገው የደመራውን በዓል እንዴት እንደተጠቀሙበት በመደጋገም ለማሳየት፤ ይህችን ጦማር ዘዳግም በሚል ርእስ ሰየምኳት። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ቅኔና አዘማሪ

ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር፤ ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ። ስለዚህ አዘማሪ ወደሚለው ቃል ዘው ብለን ከመግባታችን በፊት፤ የአዘማሪን ተልእኮ መዳሰስ ሊኖርብን ነው። አዘማሪ የሚለው ቃል የግብር (የተልእኮ) መግለጫ ነው። ተልእኮውም ራሱ አዘማሪ ተቀኝቶም ሆነ፤ ገጥሞ ወይም ሌላ የተቀኘውን በዝማሬው ቅላጼ ከጉሮሮውና ከመሳሪያ ጋራ አስማምቶ፣ ቀምሞ፤ አስወድዶና አስውቦ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ህዝቡንም፤ ከባህሉ፡ ከታሪኩ፡ ከኢትዮጵያዊነቱና ከስሜቱ ጋራ ማገናኘት ነው። እርስ በርሱም ያቀራርባል። ያዋህዳል። ያስተባብራል። እንደ ኢትዮጵያ ከመሰለ በቅኝ ግዛት ሳይወረር የራሱን ጠብቆ ከሚኖር አገር የሚፈልቅ አዘማሪ የሰሚን ስሜት እያስረቀረቀ የሚያስተላልፈው ቅኔ፦ ኅብር፤ ሰምና ወርቅ፤ ሰረዝ፤ ጎዳና፤ ውስጠ ወይራና ሌላም ዓይነቶች አሉ። ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ላለማድረግ፤ ስለአዘማሪ ከመናገሬ በፊት ስለኢትዮጵያዊ ቅኔ ትንሽ ማብራሪያ መስጠት ፈለኩ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

1 2 3 4 5 7