Category Archives: አዳዲስ ዜናዎችና መልእክቶች

እርም (ሐራም)

በባህላችን የሰው ስም በትርጉም አልባነት እንደማይለጠፍ፤ ከሰውነታችን ጋራ የሚገናኙ ነገሮችም ስማቸው ከመነሻቸው ጋራ የተያያዘ ነው። “እንጀራ” ከምድራዊ ህይወታችን ጋራ ከተገናኙት መሠረታውያን ነገሮች አንዱ ነው። እንጀራ እስካሁን ድረስ የተነሳበትን የታሪክ ትዝታ ተሸክሞ ብዙ ዘመን ተጉዟል። እንጀራ ከወላጅ እናቱ ከጤፍ ጋራ በመተባበር ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ጋራ ያላቸው ግንኙነት ሩቅና ጥልቅ ትስስር እንዳለው ሁሉ፤ ከመብላት ስሜትና ሱስ ጋራ ተዋህዶ በሰውነታችን ስለጋባ፤ ዝንት ዓለም የኖረ ይህን ጥብቅ ግንኙነት የሚያስለቅቅ፤ ጥብቅ ምክንያት መቅረብ ያለበት ይመስለኛል። ከኢትዮጵያ እየተጫነ የሚመጣውን እንጀራ አትብሉ ወደሚለው ሀሳብ ምን እንደወሰደን በግልጽ ለማቅረብና፤ እንዴትስ እናቁም ወደ ሚለው ውይይት ለመግባት፤ ከጉባዔ ትምህርት ቤት መምህራን የሰማሁትን ለውይይታችን መንደርደሪያ ብናድርገው የሚጠቅም ይመስለኛል። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

እግዚአብሔር ያሳየዎ: ክርስቶስ ያመልክተዎ!

ማህበረ ቅዱሳንና አባማትያስ
እግዚአብሔር በሚያሳየው ክርስቶስ በሚያመለክተው መስመር የማይሰለፍ፤ በቡድንና በጥቅም በተራቆተ ስሜት ተሳስሮና ተለባብሶ የሚኖር ህብረተሰብ፤ ከራሱ በሚፈልቅ ስሜት ወይም ከውጭ በሚመጣ ግፊት ከመጠፋፋት ቢያመልጥም፣ ከመለያየት ማምለጥ ፈጽሞ አይችልም። ክርስቶስም “እርስ በርስዋ የምትለያይ አገር ሁሉ ትጠፋለች። እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት አይቆምም” (ማቴ 12።5)በማለት አስጠንቅቋል። ፍረዱብን እያሉ ተቆራኝተው ሰሞኑን ወደኛ በቀረቡት በማህበረ ቅዱሳንና በአባማትያስ መካከል የተከሰተው ይህ ነው። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዘዳግም!

ሙሴ አራቱን የኦሪት መጻሕፍት ከጻፈ በኋላ፤ በአራቱም መጻሕት የገለጻቸውን ጠቅለል አድርጎ በድጋሚ ያቀረበበት አምስተኛው መጽሐፍ ዘዳግም ይባላል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሰባዊ ክብርና ልዕልና ተጻራሪ የሆነውን ለማስወገድ የገለጸባቸውን ኃይለ ቃላት ለማስጨበት “አማን አማን እብለክሙ” እያለ በመደጋጋም ተናግሯል። በጸሎተ ቅዳሴያችንም “ተንስኡ ለጸሎት” የሚለውን እንደጋግማለን። ቃጭልም በመደጋገም እናቃጭላለን። የሚደጋገሙበት ምክንያት፤ የሰው ቀልብ ባዘነጊ ነገር በፍጥነት ይሰረቃል። ለዘላቂ ህይወቱ ተጻራሪና ከንቱ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ ተንሸራቶ ስለሚገባ፤ ቀልቡንና ትኩረቱን ለመጠበቅ ነው። እንደዚሁ ሁሉ፤ እኔም አባቶቻችን የገጠማቸውን ችግር መፍቻ አድርገው የደመራውን በዓል እንዴት እንደተጠቀሙበት በመደጋገም ለማሳየት፤ ይህችን ጦማር ዘዳግም በሚል ርእስ ሰየምኳት። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ቅኔና አዘማሪ

ለአዘማሪ ሙያ ተስማሚ የግብር መግለጫ መሆን ያለበት የቱ ነው? አዘማሪ ወይስ አርቲስት? በሚል በአቶ ዓለም ነጻነት ሬድዮ የቀረበው ውይይት ለዚህች ጦማር መነሻ ሆኖኛል። ከቀደሙ አባቶች እንደሰማሁት አዘማሪ ብቻውን የቆመ አይደለም። ከብዙ ነገሮች ጋራ ከቅኔያችን፣ ከዜማችንና ከስሜታችን ጋራ የተያያዘ ነው። አዘማሪ የሚለውን ቃል ከነዚህ ነጥሎ ለማቅረብ መሞከር፤ ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ያደርገዋል የሚል ስጋት አለኝ። ስለዚህ አዘማሪ ወደሚለው ቃል ዘው ብለን ከመግባታችን በፊት፤ የአዘማሪን ተልእኮ መዳሰስ ሊኖርብን ነው። አዘማሪ የሚለው ቃል የግብር (የተልእኮ) መግለጫ ነው። ተልእኮውም ራሱ አዘማሪ ተቀኝቶም ሆነ፤ ገጥሞ ወይም ሌላ የተቀኘውን በዝማሬው ቅላጼ ከጉሮሮውና ከመሳሪያ ጋራ አስማምቶ፣ ቀምሞ፤ አስወድዶና አስውቦ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ህዝቡንም፤ ከባህሉ፡ ከታሪኩ፡ ከኢትዮጵያዊነቱና ከስሜቱ ጋራ ማገናኘት ነው። እርስ በርሱም ያቀራርባል። ያዋህዳል። ያስተባብራል። እንደ ኢትዮጵያ ከመሰለ በቅኝ ግዛት ሳይወረር የራሱን ጠብቆ ከሚኖር አገር የሚፈልቅ አዘማሪ የሰሚን ስሜት እያስረቀረቀ የሚያስተላልፈው ቅኔ፦ ኅብር፤ ሰምና ወርቅ፤ ሰረዝ፤ ጎዳና፤ ውስጠ ወይራና ሌላም ዓይነቶች አሉ። ያዘማሪን ክብርና ቦታ ዝቅ ላለማድረግ፤ ስለአዘማሪ ከመናገሬ በፊት ስለኢትዮጵያዊ ቅኔ ትንሽ ማብራሪያ መስጠት ፈለኩ። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የሰይጣን መፈክር በዋሸንግተን ዲሲ ቅድስት ማርያም ቤተ መቅደስ

በአገር ውስጥ የሚኖረው በውጭም የተበተነው ወገናቸው ስለአገራችን፥ ስለታሪካችንና በጥቅሉ ስለምንርባት ዓለምና አካባቢያችን እንድንማማርባቸውና እንድወያይባቸው በጥልቀት ያሰቡ ወገኖቻችን በዘረጉልን ድኅረ ገጾች በኅዳር ወር “ጠልሰም በዲሲ (እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ)” በሚል ርእስ ያዘጋጀኋት ጦማር በሰፊው ተነባለች፡፡ በመላ ዓለምና በአሜሪካ ዙሪያ፥ በተለይም በጠልሰሟ የተንጸባረቀውን ሸፍጥና ክህደት በቅርቡ የሚያውቀውን የዋሸንግተን ዲሲ ሕዝብ ከተጠበቀው በላይ በአመርቂ ሁኔታ ማርካቷን ከያቅጣጫው ከደረሰኝ የይበል ድጋፍ በሰፊው ተገንዝቤአለሁ፡፡

በጠልሰመኛው የተዘጋጀችው ጠልሰም ታሪክን ደምስሳ፥ እምነትን አቃውሳ፥ ቤተ ክርስቲያናችን ከኦሪየንታል አቻዎቿ ለይታ ያፍዝ ያደንዝዝ አዚሟን “ጠልሰም በዲሲ ደፍተራ” ብየ ባቀረብኳት ጦማር ብቻ ማካተት ስላልተቻለ፥ ይህችንና ሌሎችንም ተከታታይ ጦማሮች ማዘጋጀት ተገደድኩ፡፡ ጠልሰመኛው ከቤተ መቅደስ ለቆ እስኪወጣ ድረስ፥ ጠለሰሟ የጸንሰቻቸው በተለያዩ ርእሶች ገና የሚወለዱ ብዙ የማቀርባቸው ተከታታይ ጦማሮች አሉ፡፡ ከነሱም ውስጥ አንዷ የክርስቶስን ወደዚህ ዓለም ለኃጢአት ሥርየት መምጣቱን የካደውን ፒላጊዎስን በጠቀሰችባት አንቀጿ ሰውን ሁሉ ለማሳሳት የሞከረችበትን መፈክረ ሰይጣን የምገልጽባት ይህች ጦማር ናት፡፡ ፥ በወጣቶች ላይ አተኩራና እግር መንገዷንም በስማ በለው ለካንሳስ ደብረ
ሣህል መድኃኔ ዓለም ምእመናንን ልምከራችሁ እያለች በሰነዘረችው አዋጅ ያፍዝ ያደንዝዝ አዚም ለማዞር መሞከሯን ያነበባት ወገን ሳይታዘባት እንዳልቀረም ተረድቻለሁ፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ወደ ፈተና አታግባን

በዚህ ሰሞን ራሴን ከራሴ ያጣሁት መሰለኝና መፈለግ ጀመርኩ። በእንቅልፍ ላይ የነበርኩም መሰለኝ። ሰውነቴን ለመቀስቀስ ጎተጎትኩት፤ ከሰመመኔ ለመላቀቅ እየታገልኩ ተንጠራራሁ። ራሴንም ወዘወዝኩ። ሙሉ በሙሉ ሳልነቃ በመንፈሴ እኔነቴን ታቅፌ ወደ ተወለድኩባት መንደር፤ ፊደል ወደ ቆጠርኩባት ደብር፤ በየደረጃው ለመማር የዞርኩባቸውን ታላላቅ የጉባዔ መካናትንና መምህራንን ቃኝሁ።

ኢትዮጵያን ለቅቄ በወጣሁበት ጊዜ ከዓለም ሸሽተው የዘጉትን፤ በዓለም ላይ አኩርፈው በዝምታ ላይ የነበሩትንና፤ በሕዝብ መካከል የሚንቀሳቀሱትን ሊቃውንት ተመለከትኩ። ሁሉም የሉም። ድምጻቸው ግን ይሰማኛል። የሚሰማኝ ድምጽ የኑዛዜ ድምጽ ሆነብኝ። የስቅለት ዕለት እየሰገድን የምንተነፍሳት፤ ሥርዐተ ቁርባኑን የምንደመድምባት “አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት” የምንላትን በሰመመን እየወደኩ እየተነሳሁ ማንጎራጎር ጀመርኩ። ከዚያም መጥምቁ ዮሐንስ ትዝ አለኝ። እመቤታችን ቅድስት ድንግልም የተናገረችው፤ ከሷም በኌላ “ይእቲ ሥጋ እንተ ነስአ መድኅን እማርያም” እያሉ ያንጎራጉሩ የነበሩ ሊቃውንት ከፊቴ ተደረደሩብኝ። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ሆነው ከሚያስተጋቡት ጩኸት ጋራ ተገጣጠመብኝ። ታዲያ ከኔ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያውያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አበው ዛሬ ቢኖሩ ምን ይሉ ነበር? ይህችን ወቅትስ እንዴት ይመለከቷት ነበር? የሚል ጥያቄ ተፈጠረብኝና ይህችን ጦማር በ፯ አንቅጽ ለማቅረብ ተገደድኩ።
፩ኛ፦ የኑዛዜ ድምጽ
፪ኛ፦“ወደ ፈተና አታግባን። ከክፉ አድነን እንጅ”
፫ኛ፦መጥምቁ ዮሐንስ የተናገረውን
፬ኛ፦የጸሎተ ማርያም ትርጉም
፭ኛ፦ይህች ሥጋ (ሰብአዊነት)
፮ኛ፦ የኪዳን የቃዳሴ የማህሌቱ ይዘት ይለወጣል
፯ኛ፡የጽዋዕ ማኅበራት። ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ልማታዊ ፓትርያርክ

ተመልከት! ልማታዊ መንግስት ይሉሀል:: ሰላም በምድራቸው፤ በጎ ፈቃድ በዜጎቻቸው አዕምሮ እና ስነ ልቡና ላይ ልማትን የመሰረቱ እነዚህ የቻይና የጃፓንና የታይዋን መንግስታት ናቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የዘረጋው የልማት ግን፤ በጅብና በአህያ፤ በተኩላና በበግ፤ በጃርትና በዱባ መካከል የተዘረጋ የልማታ ተቃራኒ ጥፋት ነው።” እያሉ በማነጻጸር ያስጎበኙኝ መሰለኝ። ቀጥለውም፤ “የኢትዮጵያን ግማሽ ህዝብ ያቀፈችውን ኢትዮጵያዊቷን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን እመራለሁ ብለው ፓትርያርክ ነኝ የሚሉት “ካዲስ አበባ ወጥቼ በየገጠሩ ስዘዋወር ዓለም ያደነቀው ልማት ሲጣደፍ አየሁ” እያሉ ሲናገሩ ሰምተሀል። አንተ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በዘረጉት ያብነት ጉባዔ ተሳትፌያለሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ትክክለኛ ቄስ ነኝ የምትል ከሆነ፤ ያስጎበኘሁህን አይተህ፤ የነገርኩህን ሰምተህና ተረድተህ፤ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን መምህራን ካስተማሩህ የልማት ዘይቤ ጋራ አነጻጽረህ በክህነታዊ ሀለፊነትህ የምትለው ለማለት አትፍራ” ያሉኝም መሰለኝ።

በዚህ ስሜት ላይ ሆኘ ክታቧን ለመጨረስ ቀጥየ ሳነብ፤ በተራ ዝርዝር ሐ ላይ “የአገር ፍቅርና የሃላፊነት ስሜት” በምትለው አንቀጽ ስር፤ እኛ ኢትዮጵያውያን የተሰለፍንበት መስክ የሚጠይቀንን ሀላፊነት መውሰድ የማንችል ደካሞች መሆናችንን ለማሳየት እኒሁ የተከበሩ መምህራችን ብዙ ምሳሌዎችን ከጠቀሱ በኋል “ለበጎውም ለክፉውም ተጠያቂው ሁልጊዜ ሌላ ነው። . . . . . . . ራስን መጠየቅ፤ እውነትን መጋፈጥ መንፈሳዊ ወኔ ይጠይቃላ።” ካሏት እንደ ጦር ፍላጽ ከምትናደፈው ቃለ አጋኖ ላይ ደረስኩ።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“አባ ፋኑኤል አዲስ ተክል ናቸው” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

nigatuasteraye@gmail.com
መጋቢት ፳ ፳፻፮ ዓ.ም.

“ወኢይኩን ተክለ ሐዲሰ ከመ ኢይትዐበይ ወኢይደቅ ውስተ ፍትሀ ዲያብሎስ። (፩ኛ ጢ ፫፡፮) የክርስቶስን ትህትና ጠልቆ ያልተረዳ ክርስቲያን በዲያብሎስ ትእቢት ይሸነፋልና በመንፈሳዊ አመራር ላይ አታስቀምጥ።” አዲስ ተክል ማለት አዲስ ገና ያልበሰለ አማኝ ማለት ነው።

አባ ፋኑኤል ባዲስ ተክልነታቸው ነቢዩ ኢሳይያስ ስለ ጾም ከተናገረበት ምዕራፍ አንዲትን ሀረግ በጥሰው፤ በምእመናን እና በሶስት ቀሳውስት በቀድሞው ቄስ ታደሰ ሲሳይ ላይ የተላለፈውን ቃለ ውግዘት በቀላጤ ለማንሳት ባደረጉት ሙከራ “የከሳሾች ካህናት ጥላቻ ችግርና አለማመን ከዚህ ላይ ይጀምራል” በማለት የጻፉት ወረቀት ህዝቡን እንዳያደናብር ይህችን ጽሁፍ በማዘጃገት ላይ ሳለሁ፤ ይሄይስ አእምሮ የተባሉ ወገን “የሃይማኖት እርጅና አያድርስ” በሚል ርእስ March 9/ 20014 የጻፏትን መልእክት ሁለት ወዳጆቼ ላኩልኝ።[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል​

ጅብ-በማይታወቅበት-አገር-ሄዶ-ቁርበት-አንጥፉልኝ-ይላል! click here to open in new tab

Download the PDF file .


Download “ጅብ በማይታወቅበት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል​!” -በማይታወቅበት-አገር-ሄዶ-ቁርበት-አንጥፉልኝ-ይላል1.pdf – Downloaded 301 times – 356 kB

“ሠርግ” በጥንታዊት ኢትዮጵያ እምነትና ባህል የሠርግ ሥነ ስርዓት

በጋብቻ የሚካሄደው ዝግጅት ለምን ሠርግ ተባለ ? የሚል ጥያቄ መነሣቱ ስለማይቀር ምክንያቱን እንደመግቢያ ልጠቀምበት አሰብኩ። ምክንያቱን ግልጽ ለማድረግ ሁለት ምሳሌዎችን
በመጥቀስ እጀምራለሁ። ፩ኛ ወታደር ነው። ወታደራዊ ሠራዊት ድንበር አልፎ፤ ኬላ ጥሶ ወደ አንድ ሕብረተ ሰብ ሲገባ ሠርጎ ገባ ይባላል። ፪ኛው ደግሞ የወንዝ ጅረት ነው። አዋሽን የመሰለ ፈሳሽ ወንዝ ሄዶ የሚገባበት፤ የሚቆምበት እና የሚሰርግበት ቦታ ሠርግ ይባላል። የተጓዥ ሰብአዊ ቡድንና የፈሳሽ ወንዝ እንቅስቃሴና መዳረሻ የሚገለጽበት ሠርግ የተባለ ይህ ቃል ፤ ሁለት የተለያዩ ጾታዎች በተለያዩ ቤተሰቦች አድገው የጨዋታ ዘመናቸውን አቋርጠው ወደ ትዳር ሲገቡ፤ የገቡበት ክንውን መነሻቸው፤ እንቅስቃሴያቸውና መድረሻቸው ሠርግ ተብሎ ተጠራበት።

ሙሽራችን ድንቁ መንግሥቱ ወደ አክሊለ ብርሃን ሕይወትና ቤተሰብ ሠርጎ የገባበትን፤ ሙሽሪት አክሊለ ብርሃን ወደ ድንቁ መንግሥቱ ሕይወትና ቤተ ሰብ ሠርጋ የገባችበትን ክንውን
(ሠርግ)፤ ከእኛ በፊት የነበሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ሠርጋቸውን ባከናወኑበት፤ ኃጢአትና ነውር በሌለበት ባህላችን በዘፈን ለማከናወን በዚህ ቦታና ሰአት ተገኝተናል። ሠርግ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና ነገረ መለኮት ማስረጃ ሆኖ እንደ ምሳሌ የቀረበ እና በባህላችን ውስጥ ተካተው ከተያዙት ኢትዮጵያዊነታችን አንዱ ነው።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

1 3 4 5 6 7 8