Category Archives: Videos

ምኩራብ (Mekurab) በዘመናችን ቤተክርስቲያን ያጋጠማትን ችግር የዳሰሰ ጥልቅ ትምህርት!(Video)

ምኩራብ (Mekurab) በዘመናችን ቤተክርስቲያን ያጋጠማትን ችግር የዳሰሰ ጥልቅ ትምህርት!

በካንሳስ ደብረ ሣህል መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን፤ የካቲት 27 ቀን 2009 ዓ/ም ጾመ ኢየሱስ በገባ በሶስተኛው እሁድ የምኩራብ እለት ከቀሲስ አስተርአየ የቀረበ ትምህርት ነው።
የሳምንቱ ምንባባችን በክርስቶስ፤ በአይሁድና በሐዋርያት መካከል የተካሄዱትን ውዝግቦች አካተው የያዙ ናቸው። ውዝግቦች የተካሄዱትም በምኩራብ ውስጥ ነው። ይህ የምንቀበለው ሳምንት በምኩራብ የተሰየመውም በዚህ ምክንያት ነው። የጾምና ጸሎት ወቅት ባካባቢያችንና በሩቅ የምንሰማውን ካለፈው ከኛ በፊት ከተካሄደው ጋራ በማነጻጸር፤ በመርመር፤ እየታዘብን የሚታረመውን ለማረም፤ የሚጥቅመውን ለመጠበቅ ነው። የሳምንቱ ጸሎታችንም መመስረት ያለበት ውዝግቦችን በምንመረምርበት ዛሬ በተነበበው ወንጌል ነው። ወንጌሉን የምንተረጉመው በሐዋርያት ትምህርት በኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንት በእነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስብከት፤ ከዚያም በራሳችን ሊቃውንት አባቶቻችን ቅኔ ነው።
ባለንበት ዘመን በራሳችን፤ ባካባቢያችን፤ በደብራችን በአገራችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትና የማይፈቅደው በጳጳሳት በቀሳውስት በዲያቆናት በመነኮሳት በቆሞሳት ስም የሚፈጸሙ ወደ ቤተ ክርስቲያናችን ሰርገው የገቡትን መታረም የሚገባቸውን እንመልከት። ባጭሩ ለመጠቆም፦
በምኩራብ መካሄድ የማይገባቸው የተለያዩ የንግድ ቆሳቁሶች እንደገቡ፤ በቤተ ክርስቲያናችን መከሰት የሌለባቸው ድርብርብ ነገሮች፦
1ኛ፦ የተደራረቡ የቅጽል ስሞች
2ኛ፦በተለይ በውጭ ዓለም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ህንጻ ድርብ እየተባሉ የሚነገሩ ጽላቶች።
3ኛ፦በዝሙት በዘረፋ የሚወቀሱት ጳጳሳት መነኮሳት ቀሳውስት ያላንዳች ሀፍረት በድፍረት በቤተ መቅደስ አገልግሎት መሰለፋቸው።
4ኛ፦ መታረም ይገባል ከሚሉት ሰዎች ጋራ ከመተባበር ይልቅ፤ እንዲቀጥል የሚተባበሩ፤ ይ ታረም የሚለውን ድምጽ ለማፈን የሚተግሉት ሰዎች፤ የእምነት የታሪክ ጠላቶች ለሀገር ለእምነት ለታሪክ ለትውልድ ቀቅለው የበሉ፤ ከሚካሄደው የኃጢአት ዝቅጠት ትርፍ በመሸመት ላይ ያሉ፤ ለግል ጊዜአዊ ደስታ ብቻ ሲሉ፤ ክርስቶስን ይህን ስህተት ለመቃወም ስልጣን ማን ሰጠህ እያሉ እንደታገሉት፤ በዘመናችንም ይታረሙ ከሚሉት ጋራ ተሰልፈው መታረም የሚገባው እንዲታረም ከመታገል ይልቅ የሚተባበሩት ተከስተዋል። የመከራው ዘመን እንዲራዘም የሚመኙ ናቸው። ክርስቶ በአይሁድ ከሰነዘረው ከመድ ጅራፍ፤ እጅግ የበለጠ የእሳት ጅራፍ እንደሚጠብቸው በአጽንኦ ያስገነዝባል ፤ ቪድዮውን ይመልከቱ

“ጽድቅን ለመፈጸም ክርስቶስ ተጠመቀ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ (Video)

“ጽድቅን መፈጸም ይገባናል” በሚል ርዕስ ከ10 ዓመታት በፊት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  ያቀረቡትን ጦማር መልሰን ጥምቀትን ለሚያከብረው ህዝብ እንድናቀርብ በመጠየቃችን አቅርበነው ነበር። በዚህ ዓመት በከንሳስ መድኃኔዓለን ቤተ ክርስቲያን በዓውደ ምህረት ላይ አቅርበውታል። ያቀረቡትን ትምህርት ቤተ ክርስቲያኑ በቪዲዮ  ቀርጾታል። ትምህርቱ ኢትዮጵያ የተጓዘችበትንና አሁንም ያለችበትን ክርስቲያን፣ሙስሊምና ቤተ-እስራኤል ለሆነው ሁሉ ስለሚያሳይ ለህዝብ ለቀነዋል።

ቀሲስ አስተርአየ ያቀረቡት “The Cross and the River” በሚል ርእስ Professor Haggai Erlichና የመሳሰሉት የታሪክ ምስክሮች “ This unique legal tolerance blended well with abstract concept of Ethiopia as embodiment of humanistic justice; a country accepted and praised, even though it was non-Islamic. (25)  እያሉ ላቀረቡት ምስክርነት በጥምቀት በዓል የምናጸባርቀው መሰረት እንደሆነ የነገሩን ለሰባዊ ፍትህ ርትዕ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ለራሷ ህዝብና ለውጭው ወራሪዎች ስትገስጽበት ስትመሰክረው መኖሯን መስክረዋል።

Haggai Erlichና ሌሎችም ደራስያን ” Muhamed had respect for the monotheistic culture of Ethiopia, and he problaly even knew  some Geez words. He told his follwers;  “If you go to Abyssinia you will find righteousness  where God will give you relief from what you are suffering”(23-24) እንዳሉት፦ ሰው ሳይገሉ የሰው ንብረት ሳይዘርፉ፤ በሃይማኖቶቻቸው  ብቻ በራሳቸው ህዝብ  ለግድያ  አረቦች ሲሳደዱ፤ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን  ያቀፏቸው፤  ክርስቶስ “ጽድቅን መፈጸም ይገባል” ሲል ያወጀው  ከህገ አራዊትና ከህገ ኦሪት  የበለጠችው ቅድስና ህገ ልቡናቸው  ከ“humanistic justice” ጋራ በማዋሀዳቸው  ነበር።

ስለዚህ በዚህ ወቅት ይህን ብንመለከተው የነገረ መለኮቱን መሰረት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በጥሞና ብናዳምጠው የሚጠቅም ስለሆነ  ቀሲስ አስተርአየ በዚህ ዓመት በአውደ ምህረቱ ያቀረቡትን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  የተጠመቅን ብቻ ሳንሆን አገራችን የተጓዘችበትን ረዥም የዘመናት ጉዞ በያመቱ የምናከብረው የጥምቀት በዓል የሚያስታውሰን የሚያሳስበንና ያለንበትንም ዘመን አካቶ ስለሚያሳየን አቅርበንላችኌል።

ቅዱስ ቂርቆስ በቅድስና(በጀግንነት) እናቱን መልሶ ወለደ። በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቅዱስ (ጀግና) እናቱን ይወልዳል
ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር በቅዱስ ገብርኤል ስም የተከበረውን በዓል ምክንያት በማድረግ “ቅዱስ ገብርኤል ስነ ባሕርይ አከበረ” በሚል ርእስ በያመቱ ከሚሰበከው በተለየ መንገድ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ግንዛቤ ቀሲስ አስተርአየ አቅርበውት በተለያዩ ድረ ገጾች ቀርቦ በሰፊው ተነቦ ነበር። ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖረዎ ከፈለጉ ጽሑፉ በዚህ ድረ ገጽ እንደገና ስለቀረበ ማንበብ ይችላሉ (http://www.medhanialemeotcks.org/recent-news-and-posts/stgebreal) ። ዘንድሮ ደግሞ በቅዱስ ገብርኤል ስም በሐምሌ የሚከበረውን በዓል ምክንያት በማድረግ፤ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋል በኔ የሚያምን እኔ የምሰራውን ይሰራል። ከዚያም የበለጠ ይሰራል” ብሎ ለክርስቲያኖች የሰጠውን መመሪያ ( ዮሐንስ ወንጌል 14፡12 ) መንደርደሪያ አድርገው፤ “ቅዱስ ገብርኤል ባከበረው በዚህ ልዕለ አዕምሮ፤ ቂርቆስ እናቱን ኢየሉጣን መልሶ ወለዳት። ኢየሉጣም ለልጇ ልጅ ሆነች” ብለው ቀሲስ አስተርአየ ይህን ትምህርት አቀረቡት።
“እውነት እውነት እላችኋል በኔ የሚያምን እኔ የምሰራውን ይሰራል። ከዚያም የበለጠ ይሰራል” የሚለውን ካብራሩ በኋላ፤ “ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶቻችን፤ ልጅን ወደ አባትነት፤ እናትን ወደ ልጅነት፤አሰቃይቶ የሚገለውን የፈላውን ውሀ፡ ወደ ክብር ዝውፋንነት የቀየረውን፤ የቂርቆስን እምነትና ስነ ልቡና፤ በጽላቱ ላይ ከተጻፉት ከአሰርቱ ቃላት (ሕግጋት) አስማምተው፤ ከኢትዮጵያዊነት ስነ ባህርይ ጋራ አዋህደው በህዝብ ስነ ልቡና ላይ ቀርጹት። በዚህ ረቂቅ ስነ ልቦናዊ ስልት ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያዊነት ወታደርና የክብር ዘብ በማድረግ ኢትዮጵያን ከወራሪዎች አስጠበቁ። ዛሬ በፈተና ላይ ያለችው ኢትዮጵያ (ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን) እንደ ኢየሉጣ መልሰው እንዲወልዷት በቂርቆስ እምነት ሞራልና ስነ ልቡና የተዘጋጀ ህሊና ያላቸውን ልጆቿን ትፈልጋለች” በማለት በአውደ ምህረታችን ለኛ ያቀረቡልን ትምህርት፤ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚመለከት ስለሆነ በሩቅ ላላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይደርሳችሁ ዘንድ አቀረብንላችሁ። ተመልከቱት ለሌላውም አካፍሉት፤ አሰራጩት፤ አስተምሩት።

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ ? ክፍል ሁለት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ? ክፍል ሁለት
በካንሳስ ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።

መነሻ ጥቅስ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ከቁጥር 7 – ፍጻሜ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ ? በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ?
በካንሳስ ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።

መነሻ ጥቅስ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ከቁጥር 1 – 35

1 2