Category Archives: Videos

ቅዱስ ቂርቆስ በቅድስና(በጀግንነት) እናቱን መልሶ ወለደ። በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ቅዱስ (ጀግና) እናቱን ይወልዳል
ከዚህ ቀደም በታህሳስ ወር በቅዱስ ገብርኤል ስም የተከበረውን በዓል ምክንያት በማድረግ “ቅዱስ ገብርኤል ስነ ባሕርይ አከበረ” በሚል ርእስ በያመቱ ከሚሰበከው በተለየ መንገድ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ግንዛቤ ቀሲስ አስተርአየ አቅርበውት በተለያዩ ድረ ገጾች ቀርቦ በሰፊው ተነቦ ነበር። ሙሉ ግንዛቤ እንዲኖረዎ ከፈለጉ ጽሑፉ በዚህ ድረ ገጽ እንደገና ስለቀረበ ማንበብ ይችላሉ (http://www.medhanialemeotcks.org/recent-news-and-posts/stgebreal) ። ዘንድሮ ደግሞ በቅዱስ ገብርኤል ስም በሐምሌ የሚከበረውን በዓል ምክንያት በማድረግ፤ ክርስቶስ “እውነት እውነት እላችኋል በኔ የሚያምን እኔ የምሰራውን ይሰራል። ከዚያም የበለጠ ይሰራል” ብሎ ለክርስቲያኖች የሰጠውን መመሪያ ( ዮሐንስ ወንጌል 14፡12 ) መንደርደሪያ አድርገው፤ “ቅዱስ ገብርኤል ባከበረው በዚህ ልዕለ አዕምሮ፤ ቂርቆስ እናቱን ኢየሉጣን መልሶ ወለዳት። ኢየሉጣም ለልጇ ልጅ ሆነች” ብለው ቀሲስ አስተርአየ ይህን ትምህርት አቀረቡት።
“እውነት እውነት እላችኋል በኔ የሚያምን እኔ የምሰራውን ይሰራል። ከዚያም የበለጠ ይሰራል” የሚለውን ካብራሩ በኋላ፤ “ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አባቶቻችን፤ ልጅን ወደ አባትነት፤ እናትን ወደ ልጅነት፤አሰቃይቶ የሚገለውን የፈላውን ውሀ፡ ወደ ክብር ዝውፋንነት የቀየረውን፤ የቂርቆስን እምነትና ስነ ልቡና፤ በጽላቱ ላይ ከተጻፉት ከአሰርቱ ቃላት (ሕግጋት) አስማምተው፤ ከኢትዮጵያዊነት ስነ ባህርይ ጋራ አዋህደው በህዝብ ስነ ልቡና ላይ ቀርጹት። በዚህ ረቂቅ ስነ ልቦናዊ ስልት ኢትዮጵያውያንን ለኢትዮጵያዊነት ወታደርና የክብር ዘብ በማድረግ ኢትዮጵያን ከወራሪዎች አስጠበቁ። ዛሬ በፈተና ላይ ያለችው ኢትዮጵያ (ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን) እንደ ኢየሉጣ መልሰው እንዲወልዷት በቂርቆስ እምነት ሞራልና ስነ ልቡና የተዘጋጀ ህሊና ያላቸውን ልጆቿን ትፈልጋለች” በማለት በአውደ ምህረታችን ለኛ ያቀረቡልን ትምህርት፤ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የሚመለከት ስለሆነ በሩቅ ላላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይደርሳችሁ ዘንድ አቀረብንላችሁ። ተመልከቱት ለሌላውም አካፍሉት፤ አሰራጩት፤ አስተምሩት።

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ ? ክፍል ሁለት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ? ክፍል ሁለት
በካንሳስ ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።

መነሻ ጥቅስ የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ከቁጥር 7 – ፍጻሜ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ ? በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

ጾመ ሐዋርያት ለምን የቄሶች ጾም ተባለ?
በካንሳስ ደብረ ሣህል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።

መነሻ ጥቅስ የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 15 ከቁጥር 1 – 35

ደብረ ዘይት – ስብከት በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ April 3, 2016

ፍካሬ ኢየሱስ

መጋቢት 25 ቀን 2008 ዓ. ም.

      ይህ ሳምንት ጾመ ኢየሱስን ለጀመርንለት ወቅት አምስተኛው ሳምንት መሆኑ ነው። እንደሌሎች ሳምንታት ልዩ መጠሪያና መታወቂያ ስም አለው።  ደብረ ዘይት ይባላል። ደብረ ዘይት ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ ነው። “በስመ ሀዳሪ ይጼዋእ ማህደር” እንዲል፤ ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ ለተፈጸመው ክስተት መጠሪያ ሆኗል። አገራችን ኢትዮጵያ፤  እኛ ኢትዮጵያውያን ዜጎቿ በተከሰትንባት ኢትዮጵያ እንደተባለች ማለት ነው። በዚህ ልማድ ኢትዮጵያዊው ቅዱስ ያሬድ፤  ለክስተቱ ወይም ለፍካሬ ኢየሱሱ፤ ደብረ ዘይት የተባለው ክስተቱ የተፈጸመበት ቦታ  መጠሪያ እንዲሆነው አድርጓል።

ይሁን እንጅ በከፍተኛው ትምህርት ቤቶቻችን የሚጠራበት የውስጥ ስም  አለው። ይህም በደብረ ዘይት ላይ የተከሰተው  ፍካሬ  ኢየሱስ ነው።

ከዚህ ቀደም ቀሲስ አስተርአየ ገጠመኞችን እያንጸባረቁ  በተለያዩ  ጊዜዎች ስለ ደብረ ዘይትና ስለ ፍካሬ ኢየሱስ፦

1ኛ፦ ”ኢትዮጵያ በሶስቱ ፍካሬዎች“ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ/ም

2ኛ፦ ደብረ ዘይትና አባ ማትያስ “ዘያነብብ ለይለቡ (አንባቢ ያስተውል!)” (ማቴዎስ ፳፬፡፲፭) ሚያዝያ ፳፻፭ ዓ.ም

3ኛ፦ “እንዲህ ያለ ፓትርያርክ አይተን አናውቅም” ሰኔ ፳፻፭ ዓ.ም. ጦማሮች አቅርበው በተለያዩ   ድረ ገጾች በሰፊው ተነበዋል።

ዘንድሮም ከዚህ ቀደም በጽሁፍ ያቀረቧቸውን ሁሉ ጦማሮች በቪድዮ እንዲቀርቡ ከቅርብም በሩቅም  ከሚኖሩ ምእመናን በቀረበልን ጥያቄ መሰረት፤  ካካባቢያችን ራቅ ባሉ ስቴቶች  የሚኖሩ  ሁለት ወንድሞች  ከፍተኛውን አስተዋጽኦ  በማድረግ ስላገዙን  የቪድዮ ካሜራ ልንገዛ ችለናል። ለሁለት ሳምንታት የቀረቡት ትምህርቶች ለሙከራ ያህል በቪዲዮ ተቀድተው ተለቀዋል።  ከፍተኛውን ዋጋ የረዱንን ሁለት ወንድሞቻችንንም እያመሰግን  በመጻጉዕና በፍካሬ ኢየሱስ ላይ የቀረቡት እነዚህ ትምህርቶችን አቅርበናልና ከዚህ በታች ይመልከቱ፤ ቅን እርማተዎ፥  አስተያየተዎና  ድጋፍዎ እንዳይለየን በትህትና እንጠይቃለን። ለዚህ ዓመት ላደረሰን አምላክ  ክብር ምስገና ይግባው! አሜን።

የከንሳስ  ደብረ ሣሕል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን።

 

በካንሳስ ደብረ ሣሕል መድኃኔ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ የተሰጠ መንፈሳዊ ትምህርት።
መነሻ ጥቅስ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከቁጥር 1 – 35

1 2