በመፈተን ላይ ያለችው የከንሳስ መድኃኔ የኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ በዓል አከበረች።

በመፈተን ላይ ያለችው የከንሳስ መድኃኔ የኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አመታዊ በዓል አከበረች።

ከከንሳስ ደብረ ሣሕል መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን

ፈተናው ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ ከኛ ያልተለዩ ን የዲሲው ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መምህር አባ መአዛ እና፤  የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን መምህር አባ ኃይለ ሚካኤል  ሚያዝያ 1 ቀን ዓርብ ቀደም ብለው ለበዓለ ንግሡ ወደ ከንሳስ መጡ። ቅዳሜ ሚያዚያ 2  ጧት ለቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ውለታ የዋሉት Father Piosis Alex የቆረቆሩትን ገዳም  አብረን ጎበኘን።  በጉብኝቱ ወቅት ቀሲስ አስተርአየ  Father Piosis Alex  ለኢትዮጵኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን የሰሩትን ውለታ በማውሳት ሚከተለውን ትዝታ ተናገሩ።

የቀሲስ አስተርአየ  ንግግር

የደርግ መንግሥት ፈርሶ ኢትዮጵያ በወያኔዎች እጅ ስትወድቅ፤  አቡነ መርቆርዮስና አቡና ዜና ተከታትለው   ወደ ኬንያ ተሰደዱ። መሰደዳቸውን ስሰማ በኬንያ በነበርኩበት ትምህርት ቤት ከኔ ጋራ ይማሩ የነበሩት ኬንያውን፤ በዚያ ወቅት በኬንያ ውስጥ በ PARA Government  እና PARA church ድርጅቶች ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ኬንያውያን እና፤ በአሜሪካም  Father Piosis Alex ሌሎችም በስያትል  በኦሬገን በፖርት ላንድ  በካሊፎርንያ በአትላንታና በሙዙሪያ ይኖሩ የነበሩ፤  brotherhood በሚባል ድርጅት ስም  ይንቀሳቀሱ የነበሩ ክርስቲያኖችና  የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን ንብረታቸውን በማቅረብ እያከታተሉም በናይሮቢ ለሚገኘው ለአሜሪካ ኤምባሲ ጽ/ ቤት ባቀረቡት ጥያቄ በመጀመሪያ አቡነ ዜና ወደ ስያትል ገቡ። ቀጥለውም አቡነ መርቆርዮስ ወደ ስያትል እንዲገቡ ረዱ። በሴንት ሉስ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያንም በሳቸው ጓደኛ በFather Moses አሳሳቢነትና አጋዥነት ሲሆን።  በከንሳስ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያኖቻችም በFather Piosis Alex ጋባዥነት ወደካንሳ  መጥቼ ባገኘኌቸው በነ ወይዘሮ አሰለፈች። ወይዘሮ ነገደና በሞት የተለዩን ወይዘሮ አዛለች ነው። የ Father Piosis Alex ውለታቸው የሚዘነጋ አይደለም” ካሉ በኋላ Father Piosis Alexም  የሚከተለውን ተናገሩ።

Father Piosis Alex ንግግር

ከቀሲስ አስተርአየ ጋራ በነበራቸው  ጓደኝነትና ፍቅር ቀሲስ አስተርአየ የተናገሩትንና ሌላም ከቀሲስ አስተርአየ ጋራ ሌሎ ችም ብዙ ነገሮ ች ተካፈለናል። ወደፊትም ባለብን ክርስቲያናዊ ሀላፊነት አቅማችን የፈቀደልንን ሁሉ በጎ ነገር እናደርጋለን ካሉ በኋላ የማህበር ጸሎት ተካፈልን።  በገዳሙ ቤተ ማእድ ጸበል ጸሪቅ ከተካፈልን በኋላ፤  የገዳሙን ንብረት ሁለት ጋሻ መሬትና ያላቸውን ረዥምና አጭር እቅድ ገልጸውልን በሰላም በፍቅር ሽኝተውናል።

ማታ ጥንተ ስቅለቱንና ትንሳዔውን በማስታወስ የምሕላ ጸሎት ተደርሶ የተጀመረው ቅዳሜ ማታ የተጀመረው የበዓሉ ስርአት፤  አምና በዓርብ በርሀ ለታረዱትና አሁንም በውስጥም በውጭም  በመሞት ላይ ላሉት ያሉትን ወገኖቻችን በማሰብ፤  ጸሎተ ቅዳሴው በአባ ኃይ ለ ሚካኤል ተከናውኖ፤ የዕለቱ ትምህርት በአባ መአዛ ከተሰጠ በኌላ፤ በታቦተ ህጉ ዑደት ስርአ በዓሉ ተፈጽሟል።

የእግዚአብሔር ሕግጋት (አሰርቱ ቃላት) የተጻበት ጽላት ያለበትን ታቦት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከሌሎች በዓለም ካሉት አብያተ ክርስቲያናት በተለየ መንገድ  ለምን እንደምትጠቀምበት ለመረዳት ከፈለጉ፤  ቀሲስ አስተርአየ   ስለጥምቀት በዓል “ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው ሕግጋቶች” በሚል  ርእስ  ጥር ፩ ፳፻፮ ዓ.ም. የጻፉትን  ጦማር ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።