“ጽድቅን ለመፈጸም ክርስቶስ ተጠመቀ” የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት በዓል በኢትዮጵያውን እይታ

eotc_timketጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ውሀ በዮሐንስ እጅ እንደተጠመቀ እንኳን ክርስቲያን፤ ከክርስትና እምነት ውጭ የሆነ ሁሉ ያውቀዋል። ክርስቲያን ነኝ የሚል ሁሉ ይሰብከዋል። የጥንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አበው በሰሩልን ስርአት እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፤ ከዓለም ልዩ በሆነ መንገድ በስብሸባ በዝማሬ፤ አዛውንቱ በይባቤ፤ ሴቱ በዕልልታ፤ ጎልማሶች በሆታ ሁላችንም ጥምቀት የተሸከመችውን ጥልቅና ምጡቅ ምሥጢር በከፍተኛ ስሜት እናንጸባርቃታለን። ከጥምቀት ምሥጢር ጋራ የተወሀደውን የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ለባእድ ግልጽ አድርጎ ለማቅረብና ትውልዱን ለማስተማር ከዚህ ዘመን የከፋ ዘመን ኢትዮጵያን እና ቤተ ክርስቲያናችንን የሚገጥማቸው አይመስለኝም።

የተሸከመውን የበዓሉን መልእክት ይዘት እና ጥልቀት ለወዳጅ ለጠላት ግልጽ አርጎ ለማቅረብ ለትውልዱም ለመመስከር በቤተ መቅደሱና በአውደ ምህረቱ የምንቆም ካህናት ምን ያህል እንደገባንናብቃታችንን እንመርምር። እራሳችንንም እንጠይቅ። የጥምቀቱን ምሥጢር ከሊቃውንቱ እንደተማርኩት ከኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ ስሜት ጋራ
ተዋህዶ የኢትዮጵን ክብር ከሚያንጸባርቁት ነገሮች አንዱ መሆኑን ሲነገር ሰምቼ ቢሆን ኖሮ፤ ሰአቴን ባላጠፋሁ፤ በድረ ገጾች ያቀረቡትን ወገኖች ለማድከም ባልሞከርኩ ነበር። ክርስቶስ ሲጠመቅ የወጃት ጽድቅ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ሲደረግ ከማየውና ከምሰማው ጋራ በመጋጨቷ በኢትዮጵያውያን እይታ በሚል ርእስ ይህችን ጦማር እንዳቀርበት ተገደድኩ።።
ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ