“ጽድቅን ለመፈጸም ክርስቶስ ተጠመቀ” በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ (Video)

“ጽድቅን መፈጸም ይገባናል” በሚል ርዕስ ከ10 ዓመታት በፊት ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ  ያቀረቡትን ጦማር መልሰን ጥምቀትን ለሚያከብረው ህዝብ እንድናቀርብ በመጠየቃችን አቅርበነው ነበር። በዚህ ዓመት በከንሳስ መድኃኔዓለን ቤተ ክርስቲያን በዓውደ ምህረት ላይ አቅርበውታል። ያቀረቡትን ትምህርት ቤተ ክርስቲያኑ በቪዲዮ  ቀርጾታል። ትምህርቱ ኢትዮጵያ የተጓዘችበትንና አሁንም ያለችበትን ክርስቲያን፣ሙስሊምና ቤተ-እስራኤል ለሆነው ሁሉ ስለሚያሳይ ለህዝብ ለቀነዋል።

ቀሲስ አስተርአየ ያቀረቡት “The Cross and the River” በሚል ርእስ Professor Haggai Erlichና የመሳሰሉት የታሪክ ምስክሮች “ This unique legal tolerance blended well with abstract concept of Ethiopia as embodiment of humanistic justice; a country accepted and praised, even though it was non-Islamic. (25)  እያሉ ላቀረቡት ምስክርነት በጥምቀት በዓል የምናጸባርቀው መሰረት እንደሆነ የነገሩን ለሰባዊ ፍትህ ርትዕ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ለራሷ ህዝብና ለውጭው ወራሪዎች ስትገስጽበት ስትመሰክረው መኖሯን መስክረዋል።

Haggai Erlichና ሌሎችም ደራስያን ” Muhamed had respect for the monotheistic culture of Ethiopia, and he problaly even knew  some Geez words. He told his follwers;  “If you go to Abyssinia you will find righteousness  where God will give you relief from what you are suffering”(23-24) እንዳሉት፦ ሰው ሳይገሉ የሰው ንብረት ሳይዘርፉ፤ በሃይማኖቶቻቸው  ብቻ በራሳቸው ህዝብ  ለግድያ  አረቦች ሲሳደዱ፤ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን  ያቀፏቸው፤  ክርስቶስ “ጽድቅን መፈጸም ይገባል” ሲል ያወጀው  ከህገ አራዊትና ከህገ ኦሪት  የበለጠችው ቅድስና ህገ ልቡናቸው  ከ“humanistic justice” ጋራ በማዋሀዳቸው  ነበር።

ስለዚህ በዚህ ወቅት ይህን ብንመለከተው የነገረ መለኮቱን መሰረት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በጥሞና ብናዳምጠው የሚጠቅም ስለሆነ  ቀሲስ አስተርአየ በዚህ ዓመት በአውደ ምህረቱ ያቀረቡትን፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  የተጠመቅን ብቻ ሳንሆን አገራችን የተጓዘችበትን ረዥም የዘመናት ጉዞ በያመቱ የምናከብረው የጥምቀት በዓል የሚያስታውሰን የሚያሳስበንና ያለንበትንም ዘመን አካቶ ስለሚያሳየን አቅርበንላችኌል።